የሀገር ውስጥ ዜና

የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

By Meseret Awoke

June 22, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ መገጣጠም ጀመረ።

ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ሚኒባስ፣ መለስተኛ አውቶቡስ እና የከተማ አውቶቡስ ተሽከርካሪዎችን ማምረት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰጠኝ እንግዳው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 ሚኒባሶችን በደብረብርሃን እና ገላን ገጣጥሞ ለገበያ ለማቅረብ እየሠራ መሆኑንም ነው የገለጹት።

በደብረ ብርሃን ከተማ ለተገነባው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሸከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ 2 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉን አቶ ሰጠኝ ተናግረዋል፡፡

በዘላለም ገበየሁ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!