Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 27 ቀን ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 27 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም መንገሻ÷ በክልሉ ፈተናው በሚሰጥባቸው 270 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ 18 ሺህ 923 ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናውን ይወስዳሉ ብለዋል።

የ8ኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እና የህትመት ሥራ መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ቢንያም÷በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ፈተናው ወደ መፈተኛ ማዕከላት እንደሚጓጓዝ ተናግረዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ስኬት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version