አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2100 ከሂማሊያ የበረዶ ግግር ውስጥ 75 በመቶው ሊቀልጥ እንደሚችል ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ።
በእስያ ሂንዱ ኩሽ ሂማሊያ የሚገኘው የበረዶ ግግር ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየቀለጠ መሆኑንም ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።
በዚህም በፈረንጆቹ 2100 እስከ 75 በመቶ የሚሆነው የበረዶ ግግር እንደሰም ሊቀልጥ ይችላል የሚል ሃሳብ እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡
የበረዶ ግግሩ መቅለጥ ከሂማሊያ ተራራ በታችኛው ክፍል በሚኖሩ ወደ 2 ቢሊየን ለሚጠጉ ሰዎች አደገኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ እና የውሃ እጥረት ያስከትላል ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በሂማሊያ ተራራ አካባቢ የሚኖሩ 240 ሚሊየን ሰዎች እና ከሂማሊያ ተራራ በሚመነጨው ውሃ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦታቸውን የሚሸፍኑ 1 ነጥብ 65 ቢሊየን ሰዎች ለከፋ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ይዳረጋሉም ነው ያሉት።
እነዚህ ለዓለም ሙቀት መጨመር ምንም አይነት አስተዋፅኦ ያላበረከቱ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው ሲሉም የሪፖርቱ አዘጋጅ ቡድን አባል አሚና ማሃርጃን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከእነዚህ ሰዎች ጎን በመቆም የሚያስከትለውን አደጋ ለመቀነስ መረባረብ ይገባዋል ማለታቸውን የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡
በካትማንዱ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የተቀናጀ የተራራ ልማት ማዕከል ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርት ፥ በቀጣዮቹ ዓመታት የሙቀት አማቂ ጋዞች በከፍተኛ ሁኔታ ካልቀነሱ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ እና የሙቀት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር አስጠንቅቋል።
በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በበረዶ የተሸፈነው የምድራችን ክፍል በክፈተኛ ሁኔታ መጎዳቱን እና የበረዶ ግግር የቅልጠት መጠን በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩን የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ።
እንደ ማሳያም የዓለማችን ረጅሙ ተራራ ኤቨርስት የ2 ሺህ አመታት የበረዶ ግግሩን በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በ30 አመታት ውስጥ ብቻ ማጣቱን ተመራማሪዎቹ ጠቅሰዋል።
እንደ ተመራማሪዎቹ ዓለማችን አሁን ባለው የብክለት መጠን ከቀጠለች የሂማሊያ ተራራ የበረዶ ግግርን ጨምሮ በርካታ የምድራችን የበረዶ ግግር አብዛኛው ቀልጦ ያልቃል።
ይህ መሆኑ ደግሞ ከከፍተኛ የሙቀት መጠን ባለፈ ለከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ይዳርጋል።