አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ ንቅናቄው አጋዥ የኦዲት ባለሙያዎች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ በተከናወኑ የኦዲት ሥራዎች መንግስት ሊያጣ የነበረውን በቢሊየን የሚቆጠር የታክስ ገቢ ማግኘት ተችሏል ብለዋል፡፡
በ2015 በጀት ዓመት11 ወራት መንግስት 7 ሺህ 719 የግብር ከፋዮችን ኦዲት በማድረግ ÷ 45 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ለአብነት ገልጸዋል ።
አሁንም የኦዲት ሥራችን መድረስ በቻለው ልክ ሁሉንም ግብር ከፋዮች ተደራሽ ማድረግ ባለመቻሉ መሰብሰብ ሲኖርበት ያልተሰበሰበ ገቢ መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ባለፈ በየዓመቱ የታቀደውን የገቢ ዕቅድ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳካት መቻሉን አንስተዋል፡፡
የታክስ ምጣኔም ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ጋር ያለው ጥምርታ ሲታይ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ለማሻሻል ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መሥራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡
14 የተለያዩ በዋነኛነት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እና ከ200 የሚበልጡ የውጭ ኦዲተሮች እንዲሁም የታክስ ኦዲተሮች በመድረኩ እየተሳተፋ ነው፡፡
መድረኩ “የግብር ለሀገር ክብር” ከየካቲት 2015 እስከ የካቲት 2016 የሚዘልቀው የግብርና ታክስ ሕግ ተገዥነት ንቅናቄ አካል ነው።
በበረከት ተካልኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!