Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በወላይታ ዞን ሁለተኛው ዙር ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ሁለተኛው ዙር ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ እየተካሄደ ነው።

በዞኑ የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ነዋሪዎች በመሰለፍ ድምፅ መስጠት ጀምረዋል።

በዞኑ 12 ጊዜያዊ የምርጫ ማስተባበሪያ ማዕከላት 1 ሺህ 812  የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ።

በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኙ 192 የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በሠላማዊ መንገድ ድምፁን እየሰጠ እንደሚገኝ ሪፖርተሮቻችን ተመልክተዋል።

ይህ ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ከዚህ በፊት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ. ም በስድስት ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ተካሄዶ የነበረ ሲሆን፥ በወላይታ ዞን በወቅቱ በተፈፀሙ የህግ ጥሰቶች ሳቢያ ተሰርዞ በድጋሚ እየተደረገ ይገኛል።

በመለሰ ታደለ፣ ማስተዋል አሰፋ እና ኢብራሒም ባዲ

Exit mobile version