Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ11 ወራት ወደ ውጭ ከተላከ ቡና ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 11 ወራት ወደ ውጭ ከተላከ 210 ሺህ ቶን ቡና ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡

ከዕቅዱ አንፃር ለውጭ ገበያ የቀረበው ምርትና የተገኘው ገቢ በተወሰነ መጠን ቅናሽ ቢያሳይም ከችግሩ አንፃር የተገኘው ውጤት ጥሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በጀት ዓመት ጥራትን መሠረት ያደረገ ሥራ በመሥራትና የገበያ መዳረሻዎችን በማስፋት የተሻለ ገቢ ለማግኘት በርካታ ሥራዎች እንደሚከናወኑም ነው ለኢዜአ የገለጹት፡፡

በተለይ ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ፣ ጥራትን የማስጠበቅ፣ ግብይቱን የማዘመንና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት 300 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version