የሀገር ውስጥ ዜና

የአትሌት ለሜቻ ግርማ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ድል የዓለም ክብረ ወሰን ሆነ

By Alemayehu Geremew

June 13, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለሜቻ ግርማ በፈረንጆቹ የካቲት 15 ቀን 2023 በፈረንሳይ የቤት ውስጥ የ3 ሺህ ሜትር ውድድር ያስመዘገበውድል የዓለም ክብረ ወሰን ሆኖ ፀደቀ፡፡

የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ እንዳመላከተው÷ አትሌት ለሜቻ ውድድሩን 7 ደቂቃ ከ23 ሠከንድ ከ81 ማይክሮ ሠከንድ በመግባት ያስመዘገበው ድል ነው የዓለም ክብረ-ወሰን ሆኖ የጸደቀው፡፡