አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቴክኖ ሞባይል የስፓርክ 10 ፣ የስፓርክ 10 ሲ እና የስፓርክ 10 ፕሮ ሞዴሎችን ዛሬ በሀዋሳ ከተማ አስተዋውቋል፡፡
ኩባንያው በሀገር ውስጥ በገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ ባላፉት በርካታ አመታት ቴክኖ ስልኮችን በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል።
በዚህም የውጪ ምንዛሬ በማስገኘት የቴክኖሎጂ ሽግግር በማዳበር ለሺዎች የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ ሚና አየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ኩባንያው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ በሀገር ደረጃም ከፍተኛ ግብረ ከፋይ ሆኖ እየሰራ ይገኛልም ነው የተባለው።
ስፓርክ 10 ሲረየስ ስልክ ሞዴሎች በባለ 50 እና 32 ሜጋ ፒክስል የፊትና የኋላ ካሜራዎቹ ድንቅ ምስሎችን እንዲያነሱ ታስቦ በተሻለ ጥራት የተሰሩ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡
ኩባንያው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ70 በላይ ዓለም አቀፍ ገበያዎች ላይ ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች እያደረሰ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
በታመነ አረጋ እና መርያማ በቀለ