ዓለምአቀፋዊ ዜና

የታይዋን የአየር ፣ የምድር እና የባሕር ኃይል በተጠንቀቅ እንዲጠብቁ ታዘዙ

By Meseret Awoke

June 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ታይዋንን እና ቻይናን በሚለየው ሰርጥ አካባቢ 10 የቻይና የጦር አውሮፕላኖች ታይተዋል በሚል የአየር ፣ የምድር እና የባሕር ኃይሏ ክትትል እንዲያደርግ ታይዋን አዘዘች፡፡

በዚህም መሠረት የጦር አውሮፕላኖቿ ፣ መርከቦቿ እና የምድር ሚሳኤሎቿ በተጠንቀቅ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል፡፡

ታይዋን ከሣምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 37 የሚደርሱ የቻይና የጦር አውሮፕላኖች ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ብላ ስታሳውቅ ይህ ሁለተኛ ጊዜ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!