አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የብሩህ ኢትዮጵያ 2015 ብሔራዊ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ሰኔ 4 እና 5 እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ብሩህ ኢትዮጵያ 2015 ብሔራዊ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በቡራዩ ተሰጥዖ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓም በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።
ማብቃትን መሠረት ያደረገው ይህ የውድድር መርሃ ግብር በይፋ ከተጀመረበት ዕለት ጀምሮ ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሀሳባቸውን ይበልጥ ለማጎልበትና ለውጤት ለማብቃት የሚያስችል ስልጠና ሲሰጣቸው ቆይቷል።
200 ተወዳዳሪዎች የተካፈሉበትና ሶስት ዙሮች ያሉት ይህ ውድድር የመጀመሪያው ዙር ሰኔ 4 እና 5 ቀን 2015 ዓም እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በሁሉም ዙሮች ከሚለዩ 70 የፈጠራ ሀሳቦች መካከል 50 ምርጥ ሀሳቦች እያንዳንዳቸው 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ።