አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የ2 ቢሊየን ዶላር ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ለዩክሬን እያዘጋጀች መሆኑን ይፋ አድርጋለች፡፡
የሚላከው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ዩክሬን በሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ላይ መጠነ ሠፊ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ መውሰድ መጀመሯን ተከትሎ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ፔንታገን በሚልከው የአሁኑ የሁለተኛ ዙር ድጋፍ ÷ ሁለት ዓይነት ሚሳኤሎች እንደሚያካትት ብሉምበርግ ዘግቧል።
ከዚህ ሣምንት በኋላ ከጠላት የሚወነጨፉ የባላስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን የማክሸፍ እንዲሁም የጦር አውሮፕላኖችን የመምታት ብቃት ያለው “ፒ.ኤ.ሲ- 3” የተሰኘ ዘመናዊ ሚሳኤል እና ሌላ በትዕዛዝ የሚመራ ዘመናዊ ሚሳኤል ለዩክሬን እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡
አሜሪካ በፈረንጆቹ 1960 ወደ አገልግሎት ያስገባችውን (ኤም. አይ. ኤም 23) ሚሳኤልም ዳግም አድሳ ለዩክሬን ለመላክ መዘጋጀቷን ነው ያስታወቀችው፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ÷በዚህ ወር መጀመሪያ ወታደራዊ ኃይላቸው ወደ ማጥቃቱ ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን እና የምዕራባውያኑን የጦር መሣሪያ ድጋፍም አብዝተው እንደሚሹ ለወል ስትሪት ጆርናል ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!