የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ገባ

By Melaku Gedif

June 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ ሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ገብቷል፡፡

ልዑካኑ ኪንግ ካሊድ አውሮፕላን ማረፊያ ሲድርስ የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በሳዑዲ ዓረቢያ የኢፌዴሪ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ እና የኤምባሲው ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በሳዑዲ በሚካሄደው አይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድንን ለመዋጋት ከተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው ሪያድ የገቡት፡፡