አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ጋር መከሩ፡፡
ውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአገራቱ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው ለመስራት መስማማታቸውም ተገልጿል፡፡