አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ1 ሺህ 444ኛው የሐጅ ተጓዦች ብቻ የሚውል መስገጃና ማረፍያ ያለው ተርሚናል አዘጋጅቶ የመጀመረያውን በረራ ዛሬ አስጀምሯል፡፡
በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ እና የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ያደቻ ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የአየር መንገዱ የኦፕሬሽን ዘርፍ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ ረታ መላኩ እና ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!