አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ማህበራዊ ልማትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የጃፓን መንግስት እንደሚደግፍ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ገለጹ።
በጌዴኦና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች አጎራባች አካባቢዎች ማህበራዊ ልማትና መስተጋብርን የሚያጎለብት ፕሮጀክት ዛሬ በዲላ ከተማ ይፋ ሆኗል።
ፕሮጀክቱ ከጃፓን መንግስት በተገኘ 83 ሚሊየን ብር ድጋፍ በቀጣይ ሦስት ዓመታት በዞኖቹ ባሉ አራት አዋሳኝ ወረዳዎች የሚተገበር ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፕሮጀክቱ ይፋ ሲደረግ አምባሳደር ኢቶ ታካኮ እንዳሉት ÷ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ማህበራዊ ልማትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ሥራዎችን ለማገዝ የጃፓን መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።