Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።

ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ሥራ አሥፈፃሚ አባል አቶ ግርማ የሺጥላ የሕሊና ፀሎት በማድረግ ነው።

ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ለውይይት በተዘጋጁ ሠነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላውን ሕዝብ በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ እንደሚመክር ከፓርቲው ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version