የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ  ተካሄደ

By Mikias Ayele

May 28, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በአሶሳ ከተማ በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተብ ክፍሎች ለሰራዊቱ ያላቸውን አለኝታነት ገልፀዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች መተኪያ የሌለውን ውድ ህይወቱን ሰጥቶ ሀገርን ለሚያስቀጥለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡