አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ዜጎች ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ድጋፍ በታላቅ ሠላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።
በሀዋሳ ከተማ ሰልፉ የተካሄደ ሲሆን ÷ከከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፋቸውን ገልፀዋል ፡፡
ከህብረ ብሄራዊ ሰራዊታችን ላይ እጃችሁን አንሱ፣እሱ ሞቶ እኛን ያዳነንን ሰራዊት ማጠልሸት ይቁምና ሌሎች ሰልፈኞቹ እያሰሙ ከሚገኙት መፈክር ይጠቀሳል፡፡