አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ማጠናቀቂያ ገቢ አደረጉ።
የአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘመን ጁነዲን ከክፍለ ከተማ የፅህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር በገቢ አሰባሰብ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የግድቡን ዘጠነኛ አመት መሰረት በማድረግ ታቅደው የነበሩ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን ማከናወን አለመቻሉን ገልጸዋል።
በከተማዋም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን የመከላከል ስራ እንዳለሆኖ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግድብ ግንባታ ሀብት ከማሰባሰብ ጎን ለጎን የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ለሕብረተሰቡ ስለ ግድቡ ወቅታዊ መረጃዎችን ተደራሽ የማድረግ ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አመራር እና አባላት ደም ለግሰዋል።
መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ነው
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision