Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዓለም የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የትምህርት ትብብር ድርጅት ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ በዛሬው ዕለት በይፋ ከፈተ።

በሥነ-ሥርዓቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ መንሱር ቢን ሙሳላም እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የዋና መስሪያ ቤቱ ስራ መጀመርም ኢትዮጵያ ከዓለም የትምህርት ትብብር ድርጅት ጋር ያላትን ትብብር ለማሳደግ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version