አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሶማሊያ በምዕራባውያን ተደግፋ ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት ማረጋገጥ አትችልም ሲሉ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኸ ሞሀሙድ ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት ፥ መንግስታቸው በሀገሪቱ ባለጠጋዎች እና ኩባንያዎች ላይ ከፍ ያለ ቀረጥ ለመጣል ተዘጋጅቷል፡፡
ሶማሊያ ከፍተኛ የዕዳ ጫና እንዳለባት አስታውሰውም ፥ ከእንግዲህ የእንግሊዝን ፈገግታ ፣ የአሜሪካንን ይሁንታ አልያም የዐረብ ባሕረ – ሰላጤ ሀገራትን ችሮታ እንደወትሮው ልናገኝ አንችልም ነው ያሉት፡፡
በመሆኑም መንግስት የሀገር ውስጥ የታክስ ገቢን ለማሻሻል ዝግጅት ስለማጠናቀቁ ይፋ አድርገዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ እንዳሉትም ፥ የሶማሊያ መንግስት በአዲሱ ዕቅዱ መሠረት በባለጠጋ እና በድኽነት ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች መካከል እየተስተዋለ ያለውን ኢፍትሐዊ የገቢ ልዩነት ለማመጣጠን ይጥራል፡፡
በሶማሊያ የ30 ሺህ ዶላር መኪና እና አንድ አይፎን የስልክ ቀፎ ላይ የሚጣለው የታክስ ክፍያ አንድ ዓይነት መጠን መሆኑን ጠቁመው ፥ እንዲህ ያለውን ያልተመጣጠነ አሠራር ለማስተካከል መዘጋጀታቸውን ነው ይፋ ያደረጉት፡፡
ጋሮዌ ኦንላይን እንደዘገበው ፥ የሶማሊያ የዚህ ዓመት የበጀት ዕቅድ 967 ሚሊየን ዶላር ገደማ ነው፡፡
ሁሉንም ማለት በሚቻል ደረጃ አውሮፓ ኀብረት፣ አሜሪካ ፣ ኤመሬትስ ፣ ቱርክና ተመድ ናቸው የሚሸፍኑላት፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት እንደሚለው ከሆነ ፥ ከሶማሊያ መንግስት ይልቅ አል-ሸባብ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች በህገወጥ መንገድ አስገድዶም ይሁን እንጂ የሚሰበስበው ታክስ ብልጫ አለው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን