የሀገር ውስጥ ዜና

የአርቲስት ሒሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሰኞ ይፈጸማል

By Tamrat Bishaw

May 13, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ሒሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር የፊታችን ሰኞ ጉለሌ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እንደሚፈጸም የቀብር ስነ ስርዓት አስፈጻሚ ኮሚቴው አስታውቋል።

ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ÷የሒሩት በቀለ አስከሬን የፊታችን ሰኞ ሻላ መናፈሻ ጀርባ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ ሽኝት እንደሚደረግለት ገልጿል።

ከቀኑ 7 ሰዓት ላይም ጉለሌ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ስርዓተ ቀብሩ እንደሚፈጸም ኮሚቴው ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡