አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኦሬንጅ” የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ በዘርፉ በኢትዮጵያ የመሠማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአፍሪካ በቴሌኮም ዘርፍ ላይ የተሠማራውን የ“ኦሬንጅ” ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ጀሮም ሄኒክ በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው ÷ በኢትዮጵያ በቴሌኮሙኒኬሽኑ ዘርፍ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮች ገልጸውላቸዋል፡፡
የኢፌዴሪ መንግስት ባለፉት ሁለት ዓመታት ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በቴሌኮሙ ዘርፍ ከውጭ ባለሐብቶች ጋር ለመሥራት ያሳየውን ቁርጠኝነትም አንስተው ፤ በጋራ ሊሠሩባቸው በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡
ለአብነትም ፥ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን በኢትዮጵያ ሥራ መጀመር እና የኢትዮ ቴሌኮምን ትራንስፎርሜሽን ማንሳታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኦሬንጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀሮም ሄኒክ በበኩላቸው ፥ ኮርፖሬሽኑ በአፍሪካ የቴሌኮም ገበያ ውስጥ መዋዕለ-ንዋዩን አፍስሶ ያስመዘገበው ስኬት አብራርተዋል።
በቀጣይም “ኦሬንጅ” በዘርፉ ሥራዎቹን ዕውን ለማድረግ በሚችልባቸው ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ጊዜ ቀጥሯል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን