የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በአመታዊው የኢንቨስትመንት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

By Shambel Mihret

May 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአቡዳቢ እየተካሄደ በሚገኘው አመታዊ የኢንቨስትመንት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ የተመራ ልኡክ በአቡዳቢ እየተካሄደ በሚገኘው 12ኛው አመታዊ የኢንቨስትመንት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ በአለማቀፍ የኢንቨስትመንት ጉባዔ ላይ መሳተፍ በዘርፉ እያሳየች ላለው እድገት በርካታ እድልን የሚከፍት ከመሆኑ ባሻገር የልምድ ልውውጦችን በማድረግ የንግድ  መዳረሻዎችን እንድታሰፋ የሚያግዝ ነው ተብሏል።