Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፓኪስታን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካሃን በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራን ካሃን በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በኢስላማባድ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሀገሪቱ ወታደራዊ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ኢምራን ካሃን በሙስና ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፥ እሳቸው ግን ክሱ ፖለቲካዊ ነው ሲሉ ያጣጥላሉ።

የሀገሪቱ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ካሃን ወደ ፍርድ ቤት ግቢ በመግባት ላይ እያሉ በፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኢምራን ካሃን ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር ከጠቅላይ ሚኒስትርነት የተነሱ ሲሆን፥ ያንን ተከትሎ ተደጋጋሚ ክስ ሲቀርብባቸው ቆይቷል

በሀገሪቱ በቅርቡ አጠቃላይ ምርጫ እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡

የሀገሪቱ ጦር፥ ካሃን ተሞክሮብኛል ከሚሉት የግድያ ሙከራ ጋር በተያያዘ “መሠረተ ቢስ” ያላቸውን ክሶች ከማቅረብ እንዲቆጠቡ ሲያስጠነቅቅ ቆይቷል።

Exit mobile version