የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰአታት ለ1 ሺህ 73 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደረገ

By Tibebu Kebede

April 22, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ ባለፉት 24 ሰአታት ለ1 ሺህ 73 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ሁለት ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጸዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አንደኛው 22 ዓመት እድሜ ያለው በአፋር ክልል ገዋኔ ከተማ ነዋሪ የሆነና የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ የ54 አመት ትውልደ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ ነው።

ግለሰቡ ከአሜሪካ ከመጣ ጀምሮ በለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበረ ነው።

አሁን ላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው 90 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ ሲሆኑ፥ 21 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ተገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision