አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ ሕይወት እንዲታደግ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን ደም ለግሰዋል።
በዚህ ወቅትም አንድ ላይ ሆነን ሁሉንም መሰናክሎች ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮቪድ19 ቀውስ ባለፈ አሁንም ደም የሚያስፈልጋቸውና የተለያየ የጤና እክል ያለባቸው ወገኖች መኖራቸውንም በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።
ደም ልገሳው የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የተደረገ ነው ተብሏል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision