የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ፖሊስ የመደበኛ እና አድማ ብተና የፖሊስ አባላትን አስመረቀ

By Melaku Gedif

May 06, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በ27ኛ ዙር ያሰሠጠናቸውን የመደበኛ እና አድማ ብተና የፖሊስ አባላትን አስመረቀ።

 

በምረቃ መርሐ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፖሊስ መኮንኖች መገኘታቸውን አዲስ ሚዲያ ዘግቧል።

 

ተመራቂ የፖሊስ አባላቱ በከተማዋ የሚፈፀሙ ውስብስብ ወንጀሎችን በመረዳት ቀድመው ለማክሸፍ በአካልም ሆነ በሥነ ልቦና ጠንካራ እንዲሆኑ አዳዲስ ፖሊሳዊ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸው ተጠቁሟል።