የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ለ82ኛው የዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Amele Demsew

May 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ82ኛው የኢትዮጵያ ዐርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው÷የአሁኑ ትውልድ ነጻነቷ የተከበረ ሉዓላዊት ኢትዮጵያ ባለቤት እንዲሆን አባት እና እናት አርበኞች ታላቅ ተጋድሎ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሲዘከር የሚኖር ታልቅ ድል ነው ያሉት ክንቲባዋ÷ ቀጣዩ ትውልድም የአባቶቹን ፈለግ በመከተል የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።