Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል ከ19 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል ስራ ከ19 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል፡፡
 
የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ÷በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ሺህ 422 የሳይበር ጥቃቶች እና የጥቃት ሙከራዎች መፈጸማቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ከእነዚህ መካከልም 4 ሺህ 272 ምላሽ የተሰጠባቸው እና 150 ያህሉ ደግሞ ዳት ያደረሱ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ቢደርሱ ኖሮ የመሰረተ-ልማቶችን ማቋረጥ፣ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶችን ማስተጓጎል፣ የዳታዎች መሰረቅ እና መጥፋትእንዲሁም ሌሎች ችግሮችን ይፈጥሩ እንደነበር አንስተዋል፡፡
 
የሳይበር ጥቃት ኢላማ የተደረጉትም አብዛኛዎቹ የፋይናንስ ተቋማት መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
 
የፀጥታ እና ደህንነት ተቋማት፣ ሚዲያዎች፣ ቁልፍ የመንግስት ተቋማት እና ሚኒስቴር መ/ቤቶች የጥቃት ዒላማዎች እንደነበሩ ማንሳታቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
#Ethiopia
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version