የሀገር ውስጥ ዜና

በመተከል ዞን ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪን ተቀብለው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

May 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ቆታ ቀበሌ በቀላንጤ ወገዴ የሚመራ የጉሙዝ ታጣቂ ቡድን የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም ተመለሰ፡፡

“መገዳደል ይብቃ አብሮነትና ችግሮቻችንን በውይይት እንፍታ” በሚል የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው 73 የቡድኑ ታጣቂዎች አፈሙዝ ዘቅዝቀው ወደ ሰላም የተመለሱት፡፡

የቡድኑ አባላት ወደ ሰላም ሲመለሱም÷ ከታጠቁት የቡድን እና የነፍስወከፍ መሳሪያዎች ጋር መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከመሳሪያዎቹ መካከልም ብሬን፣ አር ፒ ጂ፣ ስናይፐር እና ክላሽንኮቭን ጨምሮ ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ለቡድኑ አባላትም ወደ ግልገል በለስ ከተማ በመምጣት የክልሉ እና የዞኑ አመራሮች ባሉበት አቀባበል ተደርጎላቸው ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው ተቀላቅለዋል ተብሏል፡፡

ለሰላም የተዘረጉ እጆች ከአፈሙዝ ይልቅ በሃሳብ የበላይነት ያመኑ መሆናቸውም በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!