ቢዝነስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን ለህክምና ቁሳቁስ ማጓጓዣነት በስፋት ማሰማራቱን ገለፀ

By Tibebu Kebede

April 21, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ጭነት አገልግሎቱን ለህክምና ቁሳቁስ ማጓጓዣነት በስፋት ማሰማራት መጀመሩን ገለፀ።

አየር መንገዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫው፥ በዓለም ላይ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ተከትሎ የጭነት ማጓጓዣ (ካርጎ) አውሮፕላን ፍላጎት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል።