ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

By Amele Demsew

May 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

መሐመድ ኑር ናስር ለኢትዮጵያ ቡና ሁለቱንም ግቦች ሲያስቆጥር÷ ለአዳማ ከተማ ደግሞ ደስታ ዮሐንስ በፍጹም ቅጣት ምት እንዲሁም አድናን ረሻድ በጨዋታ አስቆጥረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ31 ነጥብ ከነበረበት7ኛ ደረጃ ወደ 5ኛ ከፍ ሲል አዳማ ከተማ ደግሞ31 ነጥብ የግብ ክፍያ ብልጫ ተወስዶበት ደረጃውን ከ8ኛ ወደ 6ኛ ከፍ አድርጓል።

በተመሳሳይ ባህር ዳር ከተማና አርባ ምንጭ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ፍራኦል መንግስቱና ፉአድ ፈረጃ ለባህር ዳር ከተማ ግቦቹን ሲያስቆጥሩ÷ እንዳልካቸው መስፍንና አሕመድ ሁሴን ለአርባ ምንጭ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡