የሀገር ውስጥ ዜና

ኮቪድ 19 በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን የከፋ ጫና ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ ይገባል- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

April 21, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ19) በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን የከፋ ጫና ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት፥ የሠራተኞችን የሥራ ዋስትናን ማስጠበቅ፣ ዘላቂ በሆነ መልኩ ገቢ እንዳይቋረጥ ማድረግ፣ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን የማኅበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ የሚያደርጉ አሠራሮችን ማስፋፋት፣ የመሠረታዊ አቅርቦቶችን የግብይት ሥርዓት ማርጋት፤ እንዲሁም ለአምራች ዘርፎች ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል።