የሀገር ውስጥ ዜና

የጀርመኑ መራሂ መንግስት በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

By Amele Demsew

April 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ፡፡

መራሂ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በውይይታቸውም ፥ ስለሰላም ስምምነቱ አተገባበር እንዲሁም አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በተለይም በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገው ይመክራሉ ተብሏል፡፡