Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከቡና፣ የሻይና ቅመማቅመም ምርቶች ከ907 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና፣ የሻይና ቅመማቅመም ምርቶች 907 ነጥብ 56 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገለጸ።

ገቢው የተገኘው ለውጭ ገበያ ከቀረበው ከ169 ሺህ ቶን በላይ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ምርቶች መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጀርመን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አሜሪካ፣ ኬንያ፣ ብሪታኒያ፣ ቻይና፣ ሕንድ እና ሌሎች ሀገራት የምርቶቹ መዳረሻዎች መሆናቸውን በባለሥልጣኑ የገበያ ልማትና ፕሮሞሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ካሳሁን ገለታ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ቀሪ ሦስት ወራት ደግሞ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ምርቶችን በጥራትና ብዛት ለውጭ ገበያ በማቅረብ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሠራ አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version