አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኮሞሮስ ዋና ከተማ ሞሮኒ ገብተዋል።
አቶ ደመቀ ሞሮኒ ሲደርሱ የኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሂር ዱልከማል ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ዛሬ ረፋድ ላይ ከኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በአራት የአፍሪካ ሀገራት የሚየደርጉትን ጉብኝት ትናንት በታንዛኒያ መጀመራቸው ይታወሳል፡፡