አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት የዲጂታል የነዳጅ መክፈያ ስርዓቶችን አስተዋውቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ÷ አንደኛው በባንኩ ሲ ቢ ኢ(CBE) ብር መክፈል የሚቻልበት ስርዓት ሲሆን ሁለተኛው ተጨማሪ ነዳጅ የሚል መተግበሪያ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ክፍያ ስርዓቶቹ የክፍያ ስርዓትን በማዘመን ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ ገንዘብ ለማሳተም የምታወጣውን ወጪ እንደሚቀንሱም ተመላክቷል።
የዜጎችን የቁጠባ ባህል ያዘምናሉ የተባሉት ሁለቱ ክፍያዎች ከከፋዮቹ የባንክ አካውንት ጋር የሚያያዙ መሆናቸውም ነው የተገለፀው፡፡
ሁለቱ የክፍያ ስርዓቶች በአዲስ አበባ የተጀመሩ ሲሆን በቀጣይ በክልሎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተጠቁሟል፡፡
በፈቲሃ አብደላ