አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መንግሥት እና ህወሓት ያደረጉት የሰላም ስምምነት ለሌሎች አፍሪካውያን ማሳያ ነው ሲሉ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና በስምምነቱ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ኡሁሩ ኬንያታ ተናገሩ፡፡
በወዳጅነት አደባባይ እየተካሔደ በሚገኘው ‘ጦርነት ይብቃ፤ ሰላም እናጽና’ የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ይህ ቀን የኢትዮጵያውያን የሰላም ቀን ነው ብለዋል፡፡
እረጅሙ የሰላም ማስፈን ሂደት በስኬት ተጠናቆ ለዚህ መብቃት በመቻሉ በሂደቱ ተሳታፊ የነበራችሁ ሁሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሆነው ለተቀረው የአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ማሳያ ነው ያሉት ኡሁሩ÷ አፍሪካ ለዘላቂ ሰላሟ እንደትሠራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!