አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 10፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የለይቶ ማቆያ አስተባባሪ ኮሚቴ በአዲስ አበባ 2500 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ቦታዎችን ተረከበ፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ ÷ ኮሚቴው 2 ሺህ አምስት መቶ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ቦታዎችን በአዲስ አበባ መረከቡን በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡
እነዚህም መገናኛ አካባቢ ያለ የአትሌት መሰረት ደፋር አዲስ ዘመናዊ ሀንፃ እና የፌደራል ቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጥና ኢንስቲትዩት መሆናቸውን ነው የጠቆሙት።
ወይዘሮ አዳነች አያይዘውምለድጋፋችሁና ለደግነታችሁ ለሁላችሁም ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!