ዓለምአቀፋዊ ዜና

ጀርመን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለፀች

By Meseret Demissu

April 18, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ጀርመን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገለፀች።

የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጄንስ ስፓሀን፥  ወረርሽኙ በቁጥጥር ለመዋሉ ዋነኛው ምክንያት ለአንድ ወር የተለያዩ  እንቅስቃሴዎች ላይ እገዳ መጣሉ ነው ብለዋል።

ሆኖም የእንቅስቃሴ ገደቡ ከግዛት ግዛትይለያይ እንደነበርም ነው የጠቀሱት።

በአውሮፓውያኑ ከሚያዝያ 12 ጀምሮ ከወረርሽኙ የሚያገግሙ ሰዎች ቁጥር በተከታታይ በቫይረሱ ከሚያዙ አዳዲስ ሰዎች ቁጥር መብለጡን ተናግረዋል።

በሀገሪቱ አዳዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 0 ነጥብ 7 በመቶ መውረዱም ነው የተነገረው።

በጀርመን በኮቪድ 19 ወረረሽኝ 3 ሺህ 868 ሰዎች ያለፈ ሲሆን፥ 134 ሺህ ያህል ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

በሀገሪቱ  የተመዘገበው የሰዎች ሞት ቁጥር በጣሊያን፣ ስፔን ወይም ፈረንሳይ ከተመዘገበው ያነሰ ነው።

ይህንን ተከትሎ የሀገሪቱ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የተጣሉ ገደቦችን የመቀነስ እርምጃዎች መውሰድ እንደሚጀመር ጠቁመው፥ መለስተኛ ሱቆች በሚቀጥለው ሳምንት ሲከፈቱ ትምህርት ቤቶችም በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ስራ መከፈት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።

አያይዘውም የሃይማኖታዊ አገልግሎቶችን ጨምሮ ትልቅ የሕዝብ ስብሰባዎች እስከ ቡና ቤቶች ፣ ካፌዎች ፣ ምግብ ቤቶች ፣ ሲኒማ ቤቶች እና የሙዚቃ ሥፍራዎች ሁሉ እስከ ነሐሴ 31 ድረስ ተዘግተው እንደሚቆዩ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision