አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የትንሳኤን እና የኢድ አልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ አልባሳት፣ የምግብ ነክ ፍጆታዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረጉ፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ የድጋፍ ስራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ አቅመ ደካሞችን በመርዳት እያደረጉ ያለውን በጎ ተግባር አድንቀው÷ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ለሁለቱም በጎ አድራጎት ድርጅቶች የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ ግምታዊ ዋጋው ከ52 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን ገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለመቄዶንያ ከ31 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም ለባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ አልባሳት እና ምግብ ነክ የፍጆታ እቃዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡