ቢዝነስ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እና ፀሐይ ባንክ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

By Alemayehu Geremew

April 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እና ፀሐይ ባንክ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት÷ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ወንድማገኘሁ ነገራ እና የፀሐይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ያሬድ መስፍን ናቸው፡፡

አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ ÷ ፀሐይ ባንክ የድርጅታቸው 22ኛ የክፍያ አጋር መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዘመናዊ የክፍያና ርክክብ ሥርዓቱን በቴክኖሎጅ በመታገዝ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ዘርግቶ ከአጋር አካላት ጋር እየሠራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ለመፍጠር የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት እንደሚያግዝ ዕምነታቸውን ገልፀዋል።

አቶ ያሬድ መስፍን÷ ባንኩ በሥምምነቱ መሠረት ለአምራቹ፣ ለአቅራቢውና ላኪው (ለሁሉም የገበያው ማኅበረሰብ) በዘመናዊ መንገድ የግብይት ሥርዓት መፈፀም ለማስቻል ይሠራል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አገልግሎቱን ለማሳለጥ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍና ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሚሰጥም ነው የገለጹት፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-