የሀገር ውስጥ ዜና

አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) ከፋኦ የኢትዮጵያ ተጠሪ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

April 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር) ከተባባሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ፋራይ ዚሙድዚ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ አዲስ ከመቋቋሙ ጋር ተያይዞ ያሉ ክፍተቶችን በመለየት በተለይም በመስኖ ስታንዳርዶችና ኮዶችን በማዘጋጀት ዙሪያ በትብብር ለመስራትም መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡