አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጣልያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በታላቁ ቤተ መንግስት የክብር የእራት ግብዣ አደረጉ።
በታላቁ ቤተ መንግስት በተደረገው የክብር እራት ግብዣ ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡