አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የሰላም ጥሪን በመቀበል ትጥቅ ከፈቱ የሽብር ቡድኑ ሸኔ የቀድሞ ታጣቂዎች ጋር ተወያየ።
ብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል፥ የሽብር ቡድኑ የቀድሞ ታጣቂዎች መሳሪያ በማስቀመጥ ወደ መደበኛ ህይወት ተመልሰው በሀገሪቱ ሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ ለመሳተፍ የሰኑ ታጣቂዎች መሆናቸውን አመልክተዋል።
በውይይቱም እነዚህ የቀድሞ ታጣቂዎች በኮሚሽኑ ብሄራዊ የተሃድሶ ፕሮግራም ውስጥ ለመሳተፍ እንደተስማሙም ነው ያስታወቁት።