አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ለክልልና ለተቋማት የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ለሚዲያ ባለሙያዎች በማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና ደኅንነት ላይ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
“ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል ርዕስ በተሰጠው ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ እንዳሉት ÷ የኮሙኒኬሽን ዘርፉን ለማሻሻልና ሀገራዊ መግባባትን ለማዳበር የዘርፉን ባለሙያ አቅም መገንባት ቀዳሚው ተግባር ሊሆን ይገባል።
ሠልጣኞቹም የወሰዱት ሥልጠና መነሻ ሊሆን የሚችል ዕውቀትና ግንዛቤ ማግኘት እንዳስቻላቸው ገልጸው በቀጣይ ሰፋ ያለና በተግባር የታገዘ ሥልጠና ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በአዳማ ለአራት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ስልጠና የተለያዩ የኮሙኒኬሽን ፣ የሚዲያ እና ተያያዥ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በቀረቡ ሰነዶች ላይም ውይይቶች መደረጋቸውን ከመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው ያመለክታል፡፡