አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የተመራ ልዑክ በዛሬው ዕለት ከአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ ከመንግስት ጋር በተደረገ የሰላም ስምምነት መሰረት ትጥቃቸውን የፈቱ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም በኮሚሽኑ የተዘጋጀው የፕሮግራም ማዕቀፍ እንዲሁም የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ተልዕኮዎች፣ የውጤት ማዕከላት፣ አደረጃጀት እና የግንኙነት ስርዓት ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በምክክር መድረኩ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሴክተር መስሪያ ቤቶችና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮች መገኘታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።