አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝነት የሚደነግገው ረቂቅ አዋጅ ነጻነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያሰፍን ሆኖ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል፡፡
ረቂቅ አዋጁን በሚመለከት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይትአድርገዋል፡፡
በምክር ቤቱ የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ÷ ሀገርን በመገንባት ሂደት ምሁራን የመሪነቱን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚያሻግር ትውልድ ማፍራት ላይ በትኩረት እንዲሰሩም አሳስበዋል።
በረቂቅ ደረጃ ያለው አዋጅ ነጻነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያሰፍን ሆኖ እንደሚዘጋጅጠቁመው÷በቀጣይ በሚደረጉ ውይይቶች ተሻሽሎ የማንንም ጥቅም በማይጎዳ መልኩ ይዘጋጃል ብለዋል።
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ የቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው ÷ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ማድረግ ያስፈለገው ተቋማዊና አስተዳደራዊ ነጻነት እንዲኖራቸው መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ያለው አሰራር በሲቪል ሰርቪስ በወጡ መመሪያዎች መሆኑ ለዩኒቨርሲቲዎች የትምህርትና ተቋማዊ ነጻነት ምቹ አለመሆኑንም አንስተዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር፣ በትምህርት፣ በማህበረሰብ ለውጥ ልቀው እንዲወጡ የአስተዳደር ነጻነት ዋነኛው እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ዩኒቨርሲቲዎች የተሻለ ተልዕኮ ይዘው በይበልጥ እንዲሰሩ የሚያበረታታ እንደሆነ በውይይት መድረኩ መገለጹን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!