Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 77ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የፓን አፍሪካ አቪዬሽን ግሩፕ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 77ኛ ዓመቱን እያከበረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው አየር መንገዱ በይፋ ሥራ የጀመረው የዛሬ 77 ዓመት ነበር።

በዚህ የረጅም ጊዜ ጉዞው ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር እያስተሳሰረ ዘልቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ141 አውሮፕላኖች አፍሪካን ጨምሮ፥ አውሮፓ፣ ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ፣ እስያን በሌሎች አህጉራት የህዝብ እና የጭነት አገልግሎት ይሰጣል።

አሁን ላይም በ131 ሀገራት የበረራ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 126ቱ አውሮፕላኖች የሕዝብ ማጓጓዣ እንዲሁም 15ቱ ደግሞ የካርጎ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።

አየር መንገዱ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ የአውሮፕላኖቹን ቁጥር ከ141 ወደ 200፣ የተጓዦችን ቁጥር ደግሞ ከ13 ሚሊየን ወደ 65 ሚሊየን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version